ፎል 2025 የእንግሊዝኛ ክፍሎች

እኛ በአሌክስንዳርያ እና በፌርፋክስ የእንግሊዝኛ ክፍሎች አለን።

እባኮትን የምትማሩበትን ቦታ ይምረጡ እና በተጨማሪ ለማወቅ ይገኙ።

ALEXANDRIA

First Baptist Church of Alexandria

2932 King St
Alexandria, VA 223

የጉግል ካርታ

ቀናት: ማክሰኞ, ረቡዕ, ሐሙስ

ሰዓት፡ 9:30AM – 11:30AM 

የክፍሎች መጀመሪያ ቀን: መስከረም 9

የክፍሎች ማብቂያ ቀን: ጥር 22

ዋጋ፡ 35 ዶላር

የሕጻናት እንክብካቤ፡ በዚህ ቦታ የሕጻናት እንክብካቤ አለን።

የአሌክሳንድሪያ ምዝገባ መመሪያዎች

ለክፍሎች ምዝገባ ኦገስት 14 ይጀምራል። እባክዎን ለክፍል ለመመዝገብ ኦገስት 14 እንደገና ይመልከቱ።

(1) የተማሪ ምዝገባ ቅጽ ይሙሉ።

(2) ልጆችዎን ከእርስዎ ጋር ወደ ክፍል ይዘው የሚመጡ ከሆነ፣ ወደ ክፍል ለምታመጡት ለእያንዳንዱ ልጅ የሕፃናት እንክብካቤ ምዝገባ ቅጽ ይሙሉ።

(3) በአካል ቀጠሮ ለመያዝ መልእክት እንልክልዎታለን።

በቀጠሮው ሰአት የትኛው ክፍል ለእርስዎ እንደሚስማማ ለማወቅ በእንግሊዝኛ እንዲያነቡ እና እንዲናገሩ እናደርግዎታለን።

ትንሽ እንግሊዝኛ የሚናገሩ ከሆነ፣ ፈተናው አጠር ያለ ይሆናል፣ ወደ 30 ደቂቃ አካባቢ። ብዙ እንግሊዝኛ የሚናገሩ ከሆነ ፈተናው ረዘም ያለ ይሆናል፣ ወደ 1 ሰዓት አካባቢ።

እርዳታ ይፈልጋሉ?

እባክዎን ወደ 571-766-8078 መልእክት ይላኩ።

FAIRFAX

Redeeming Grace Church

5200 Ox Rd, Fairfax, VA 22030

የጉግል ካርታ

ቀናት: ሰኞ, ረቡዕ, አርብ

ሰዓት፡ 9:30AM – 11:30AMየክፍሎች

መጀመሪያ ቀን: መስከረም 8

የክፍሎች ማብቂያ ቀን: ጥር 28

ዋጋ፡ 35 ዶላር

የሕጻናት እንክብካቤ፡ በዚህ ቦታ የሕጻናት እንክብካቤ የለንም

የፌርፋክስ ምዝገባ መመሪያዎች

ለክፍሎች ምዝገባ ኦገስት 14 ይጀምራል። እባክዎን ለክፍል ለመመዝገብ ኦገስት 14 እንደገና ይመልከቱ።

(1) የተማሪ ምዝገባ ቅጽ ይሙሉ።

(2) እባክዎ የምደባ ፈተና ለመውሰድ እና ምዝገባዎን ለማጠናቀቅ ከነዚህ ጊዜያት በአንዱ ወደ ፌርፋክስ አድራሻ ይምጡ።

ኦገስት 27, 9:30 – 12:30
ሴፕቴምበር 3, 9:30 – 12:30
ሴፕቴምበር 5, 9:30 – 12:30

በቀጠሮው ሰአት የትኛው ክፍል ለእርስዎ እንደሚስማማ ለማወቅ በእንግሊዝኛ እንዲያነቡ እና እንዲናገሩ እናደርግዎታለን።

ትንሽ እንግሊዝኛ የሚናገሩ ከሆነ፣ ፈተናው አጠር ያለ ይሆናል፣ ወደ 30 ደቂቃ አካባቢ። ብዙ እንግሊዝኛ የሚናገሩ ከሆነ ፈተናው ረዘም ያለ ይሆናል፣ ወደ 1 ሰዓት አካባቢ።

እርዳታ ይፈልጋሉ?

እባክዎን ወደ 201-417-6425. መልእክት ይላኩ።